ትስማ ኢትዮጵያዬ
ገንዘብ ላይተምነው ሺ ዶላር ቢንጋጋ፣
ምነው? አሳነስንው የሰላምን ዋጋ።
በጅ የያዙት ወርቅ ከመዳብ ኦንዲሉ፣
የነሱን ሰጥተው የኛን እያስጣሉ፣
በኛ ሰላም እጦት ቁጭ ብለው ‘የበሉ፣
ድስኩር ሰጥተውን እኛን እያባሉ፣
ስንቱ የሀገር ልጅ ከቤት ወ’ተው አሉ፣
መለየት አቅቶን ግርዱን ከእህሉ፣
አደባለቁብን ስልጡን ነን እያሉ።
እስኪ ሰዎች ቁሙ ልጇን አጣሩኝ፣
ሰላም ሰላም ልበል ድንገት ቢሰሙኝ።
ሁላችን እንዘምር ስለ ፍቅር ብለን፣
ኢትዮጵያ እንበል በአንድነት ቁመን፣
ቋሚ ስራ አንስራ በሕይወት እያለን።
ዘር ለ’ህል እንጂ ለሰዎች አይጠቅምም፣
መባላት ለሳት ነው ከቶ በኛ አያምርም።
ሰው ከቡር ፍጡር ነው የጌታው አምሳል፣
እርሱ የሰራውን እንዴት? ሰው ያፈርሳል።
ፍቅራችን ያገግም ጠንክረን እንስራ፣
ታሪክ እንዳይወቅሰን ያባቶች አደራ፣
ቢሆን ጥሩ ነበር ታሪክ ብንሰራ፣
ባይሆንልን እንኳን ጥሩ ባንሰራ፣
ቃል ኪዳን አለብን የሀገር አደራ።
ጥላቻን በፍቅር አርገን መንዝረን፣
ካለፉት ትርክቶች ደጉን ተምረን፣
በቃ! እንዲለን ጌታ እንዲራራልን፣
ይቅር እንባባል ይቅር እንዲለን።
ገጣሚ፦ምስጋን መልካሙ
ስ.ቁ 0948821225
